ሀገር ቤት ምንድን ነው? የኢትዮጵያ አዳዲስ የተለያዩ ፊልሞች ፣ ድራማዎች እና ሲትኮሞች መገኛ
ሀገር ቤት የኢትዮጵያ መዝናኛዎችን በአማርኛ የሚያቀርብ የደንበኝነት (ሰብስክሪፕሽን) ስትሪሚንግ አገልግሎት ነው። የኢትዮጵያ ፊልሞችን፣ ተከታታይ ድራማዎችን፣ ሲትኮሞችን፣ ስታንድ-አፕ ኮሜዲዎችን፣ የልጆች አኒሜሽኖችን፣ ግጥሞችንና የምግብ ዝግጅቶችን በአንድ መተግበሪያ ያቀርባል:: አብዛኞቹ ሥራዎች የእንግሊዝኛ ንዑስ ጽሑፍ (Subtitle) አላቸው፤ ወርሀዊ ክፍያው ከ$8.99 የሚጀምር ሲሆን በየትኛውም የአለማችን አካባቢዎች በስልክ፣ በኮምፒውተርና በስማርት ቲቪ ይሰራል።
ያደጉት የኢትዮጵያ ፊልሞችንና ኮሜዲዎችን እያዩ ከሆነ፣ ወይም ልጆችዎን ከአዲስ አበባ ርቀው እያሳደጉ ከሆነ፣ ሀገር ቤት ለእርስዎ የተሰራ ነው።
ሀገር ቤት የሚለው ስም ምን ማለት ነው?
“HagerBet” የሚለው ስያሜ ከአማርኛው «ሀገር ቤት» የተወሰደ ነው፤ ትርጉሙም የትውልድ ሀገርንና ቤተሰብን የሚያስታውስ ማለት ነው። ሀሳቡ ቀላል ነው፤ የትም ቢኖሩ HagerBet በስክሪንዎ ላይ የሀገር ቤት ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርግ መተግበሪያ ነው።
“ሀገር ቤት” የተዘጋጀው ለማን ነው?
«ሀገር ቤት» በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በእንግሊዝና በአውሮፓ በሚድል ኢስት እንዲሁም በአውስትራሊያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ባህልና ታሪኮች ለሚወዱ ሁሉ የተዘጋጀ ነው።
በተለይ «ሀገር ቤት» ለሦስት ዓይነት ተመልካቾች ይስማማል፦
- በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ቤተሰቦች፦ ልጆቻቸው አማርኛ እንዲሰሙና የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ እንዲከታተሉ እድል ይሰጣል።
- ለፊልምና የድራማ አፍቃሪዎች፦ ያልተሟሉና ጥራታቸው የወረደ ቅጂዎች ለሰለቻቸው አዳዲስ ሥራዎችን እንዲከታተሉ እድል ይፈጥራል።
- ባህር ማዶ ተወልዶ ላደገው ትውልድ፦ ታሪኩን በእንግሊዝኛ ንዑስ ጽሑፍ እንዲከታተሉ ጥሩ አማራጭ ይሆናል።
«ሀገር ቤት» በ HagerBet Media FZ-LLC የሚተዳደር ሲሆን ቢሮዎቹ በዱባይና በአዲስ አበባ ይገኛሉ።
በ ሀገር ቤት ምን መመልከት ይችላሉ?
በ ሀገር ቤት ያለው ሁሉ የኢትዮጵያ መዝናኛ ሲሆን በዘጠኝ ዘርፎች ተደራጅቷል። ሀገር ቤት እያንዳንዱን ሥራዎች የማሰራጨት መብት አለው፤ በየሳምንቱም አዳዲስ የመዝናኛ የጥበብ ሥራዎችን ያቀርባል።
|
ዘርፍ |
ምንድን ነው |
ምሳሌዎች |
|---|---|---|
|
ሙሉ ርዝመት ያላቸው የአማርኛ ፊልሞች |
ሀይሌ ገገማው: 72:0 ሰዓት: አቀንቃኙ |
|
|
ተከታታይ ድራማዎች |
ፉኖስ: ግማሽ እውነት: የዘመን ፈገግታ |
|
|
የቤተሰብና የሥራ ቦታ ኮሜዲዎች |
70/80፣ ዴይ ኬር: ከተማው |
|
|
የመድረክ ኮሜዲ ዝግጅቶች |
የኢትዮጵያ ኮሜዲያኖች ዝግጅቶች |
|
|
አስቂኝ አጫጭር ፊልሞችና ቀልዶች |
አይጧ: ጉርሻ: በርበሬና ዘይት |
|
|
ለልጆች የሚሆኑ የአማርኛ ተረቶች |
ስስታሙ ነጋዴና ታማኙ ውሻ |
|
|
የአማርኛ ግጥሞችና ወጎች |
የኢትዮጵያ ገጣሚያን ሥራዎች |
|
|
የምግብ ዝግጅቶች |
ጥብስ ፍርፍር፣ የአጃ ጨጨብሳ |
የሀገር ቤት ጥበባዊ ሥራዎች ዋጋ ስንት ነው?
ሀገር ቤት ሦስት የአከፋፈል መንገዶች አሉት፤ እነዚህም ሁሉንም ስብስቦች ያካትታሉ፦
- ለ1 ወር፦ $8.99
- ለ3 ወር፦ $24.99
- ለ6 ወር፦ $48.99
ዋጋው በሁሉም ሀገሮች ተመሳሳይ ነው። የነፃ ሙከራ ጊዜ የለውም፤ በማንኛውም ጊዜ ማቋረጥ ይችላሉ። ለመምረጥ እንዲረዳዎ የሀገር ቤት ክፍያ መንገዶች ማብራሪያን ያንብቡ።
|
ለመመልከት ዝግጁ ነዎት? የ HagerBet አካውንት ይክፈቱ እና የኢትዮጵያ ፊልሞችንና ዝግጅቶችን ዛሬውኑ ይመልከቱ። |
ሀገር ቤትን እንዴት መመልከት ይቻላል?
ሀገር ቤትን በድረ-ገጽ ብራውዘር፣ በ Android እና በ iOS ስልኮችና ታብሌቶች፣ እንዲሁም በስማርት ቲቪና በ Android TV ላይ መመልከት ይችላሉ። ቪዲዮዎቹ በ HD (720p እና 1080p) ይቀርባሉ። አንድ አካውንት በአንድ ጊዜ በሁለት ዲቫይሶች ላይ ይሰራል፤ ለቤተሰብዎ አባላት የተለያዩ ፕሮፋይሎችንም መፍጠር ይችላሉ።
መተግበሪያው በሙሉ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ይቀያየራል፤ አብዛኞቹ ርዕሶች የእንግሊዝኛ ንዑስ ጽሑፍ ስላላቸው አማርኛ ገና እየተማሩ ላሉ የቤተሰብ አባላትና ጓደኞች ይመቻል። ተጨማሪ መረጃ በእንግሊዝኛ ንዑስ ጽሑፍ የሚታዩ የኢትዮጵያ ፊልሞች በሚለው ጽሑፍ ውስጥ ያገኛሉ።
ሀገር ቤት የውርርድ (ቤቲንግ) ድረ-ገጽ ነው?
አይደለም። ሀገር ቤት የፊልሞችና የዝግጅቶች ስትሪሚንግ አገልግሎት ነው። በስሙ ውስጥ ያለው «Bet» የአማርኛው «ቤት» እንጂ የእንግሊዝኛውን የውርርድ ቃል አይወክልም።
ሀገር ቤትን መጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀና ሕጋዊ ነው?
አዎ። ሀገር ቤት በሚያሰራጫቸው ሁሉም ጥበባዊ ሥራዎች ላይ ሕጋዊ መብት አለው፤ በዚህም ደንበኝነትዎ የኢትዮጵያ ፊልሞችንና የኪነጥበብ ስራን የሚሰሩ ባለሙያዎችን ይደግፋል። በሕጋዊ አገልግሎት መመልከት የኢትዮጵያ ፊልሞችን በሕጋዊ መንገድ ለማየት ቀላሉ መንገድ ነው።
አካውንትዎም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፦
- ክፍያዎች ደህንነቱ በተጠበቀ አለምአቀፍ የካርድ ክፍያ አቅራቢ (Stripe) ይስተናገዳሉ። ሀገር ቤት የካርድ መረጃዎን አያስቀምጥም።
- መግቢያው የአንድ ጊዜ የይለፍ ኮድ (OTP)፣ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA) እና ሌሎችንም አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት እርምጃዎች ያካሂዳል::
- ሀገር ቤት የግል መረጃዎን አይሸጥም ወይም አያከራይም። ዝርዝሩ በግላዊነት ፖሊሲው ውስጥ ተካቷል።
ከ ሀገር ቤት እርዳታ እንዴት አገኛለሁ?
ያግኙን በሚለው ገጽ ላይ ያለውን ቅጽ ይጠቀሙ ወይም በ info@hagerbet.tv ኢሜይል ይላኩ። የድጋፍ ቡድኑ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት (በምሥራቅ አፍሪካ ሰዓት አቆጣጠር) ይሰራል፤ በ24 ሰዓት ውስጥ ምላሽ ይሰጣል።
በሀገር ቤት መመልከት እንዴት እጀምራለሁ?
- ወደ hagerbet.tv ይሂዱ እና ይመዝገቡ የሚለውን ይጫኑ።
- የክፍያ ሁኔታውን ይምረጡ፦ 1 ወር፣ 3 ወር ወይም 6 ወር።
- በካርድ ይክፈሉ፤ የመተግበሪያውን ቋንቋ አማርኛ ወይም እንግሊዝኛ ይምረጡ።
- ማንኛውንም መዝናኛ ከፍተው መመልከት ይጀምሩ።


