የአገልግሎት ውሎች እና ሁኔታዎች
|
ሁኔታዎች እና ግዴታዎች |
|
እንኳን ወደ ሀገር ቤት ሚዲያ በደህና መጡ። የሞባይል መተግበሪያችንን ወይም ድረ-ገጻችንን አገልግሎቶች በማግኘትዎ እና በመጠቀምዎ ፣ ከዚህ በታች የተቀመጡትን ሁኔታዎች እና ግዴታዎች ለማክበር እና ውሉን ለማክበር ተስማምተዋል።
1. የደንበኝነት ምዝገባ እና ክፍያዎች - ሀገር ቤት ሚዲያ የደንበኝነት ምዝገባ አገልግሎት ነው። ዕቅዶች ለ1 ወር፣ ለ3 ወራት ወይም ለ6 ወራት ይገኛሉ። ዋጋው እንደ መተግበሪያ መደብሩ እና እንደ ሀገሩ ይለያያል፤ ከመመዝገብዎ በፊት በመተግበሪያው ውስጥ ይታያል። - ለደንበኝነት በመመዝገብዎ፣ የሃገር ቤት መድረክ የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያዎን ከመረጡት የመክፈያ ዘዴ (በመተግበሪያ መደብር መለያዎ በኩል በውስጠ-መተግበሪያ ግዢ) ላይ በራስ-ሰር እንዲቆረጥ ፈቅደዋል። - ክፍያዎች በየወሩ የሚቆረጡ በመሆናቸው ምዝገባዎን ካልሰረዙ በስተቀር ቀጣይነት ይኖራቸዋል። - በሕግ ካልተገደዱ በስተቀር ማንኛቸውም ክፍያዎች ተመላሽ አይሆኑም።
2. የደንበኝነት ምዝገባ ስምምነት - «ለደንበኝነት ይመዝገቡ» የሚለውን ጠቅ ማድረግዎ፣ መለያ መፍጠርዎ ወይም በአገልግሎታችን መጠቀምዎን መቀጠልዎ በእነዚህ ሁኔታዎች እና ግዴታዎች እንደተስማሙ ተደርጐ ይታሰባል። - የደንበኝነት ምዝገባዎን እስኪሰርዙ ድረስ ክፍያዎች በራስ-ሰር እንደሚቆረጡ አውቀው ተስማምተዋል።
3. የመለያ ተደራሽነት እና አጠቃቀም - ተመዝጋቢዎች ሀገር ቤት ሚዲያን በአንድ መለያ በተመሳሳይ ጊዜ እንደ ዕቅዱ እስከ 3 (የ1 ወር)፣ 5 (የ3 ወራት) ወይም 10 (የ6 ወራት) መሳሪያዎች ላይ መጠቀም ይችላሉ። - መለያዎች ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ አዋቂዎች ብቻ ናቸው። ልጆች ሊመለከቱ የሚችሉት በወላጅ ወይም በአሳዳጊ መለያ እና ቁጥጥር ስር ብቻ ነው። መለያዎች ግላዊ እና ወደ ሌላ የማይተላለፉ ናቸው። ከቤተሰብዎ ውጭ የመግቢያ መለያዎችን ማጋራት፣ የመለያ መታገድን ሊያስከትል ይችላል። - የመለያ ዝርዝሮችዎን ሚስጥራዊነት የመጠበቅ ሃላፊነት እርስዎ ይሆናል።
4. የይዘት ተገኝነት - በሃገር ቤት ሚዲያ ላይ ያሉ ይዘቶች በሃገር ቤት ሚዲያ የተዘጋጁ ወይም ከኢትዮጵያውያን አዘጋጆች በብቸኝነት ፈቃድ የተገኙ ናቸው። - ማንኛውም ይዘት የሚቀርበው የንግድ ላልሆነ፣ ለግል መጠቀሚያነት ብቻ ነው። ዳግም ማሰራጨት፣ መቅዳት ወይም ያለፈቃድ ማጋራት የተከለከለ ነው። - በራሳችን ውሳኔ አንድን ይዘት የማዘመን፣ የመቀየር ወይም የማስወገድ መብታችን የተጠበቀ ነው።
5. መሰረዝ እና ማቋረጥ - የደንበኝነት ምዝገባዎን በማንኛውም ጊዜ በመተግበሪያ መደብር መለያ ቅንብሮችዎ ውስጥ መሰረዝ ይችላሉ። - ስረዛ የወደፊት ክፍያን ያስቆማል፣ ነገር ግን የወቅቱን የክፍያ ዑደት ገንዘብ ተመላሽ አያደርግም። - የሃገር ቤት ሚዲያ እነዚህን ግዴታዎች እና ሁኔታዎች የሚጥሱ መለያዎችን ሊያግድ ወይም ሊያቋርጥ ይችላል።
6. ግላዊነት እና የመረጃ ጥበቃ - የግል እና የክፍያ መረጃዎ በዚህ ኢንዱስትሪ አለ በተባለ የምስጠራ (encryption) ደረጃ እና ደህንነታቸው በተጠበቁ መግቢያዎች (gateways) የተጠበቀ ነው። - ለዝርዝሩ፣ እባክዎ የግላዊነት መመሪያችንን ይመልከቱ።
7. ተጠያቂነት እና ማስተባበያ - በቴክኒክ ጉዳዮች፣ በሶስተኛ ወገን አገልግሎቶች ወይም የኢንተርኔት ግንኙነት ችግሮች ለሚፈጠሩ መቆራረጦች ሃገር ቤት ሚዲያ ተጠያቂ አይሆንም። - አንድ ይዘት ሁልጊዜ በተወሰኑ ቅርጸቶች፣ ክልሎች ወይም ቋንቋዎች ለመገኘቱ ምንም አይነት ዋስትና አንሰጥም።
8. በግዴታዎች እና በሁኔታዎች ላይ የሚደረጉ ለውጦች - የሃገር ቤት ሚዲያ እነዚህን ግዴታዎች እና ሁኔታዎች በማንኛውም ጊዜ ማዘመን ይችላል። - ከዝማኔዎች በኋላ አገልግሎቱን መጠቀም መቀጠል በተሻሻሉት ግዴታዎች እና ሁኔታዎች እንደመስማማት ይቆጠራል።
9. ያግኙን - እነዚህን ግዴታዎች እና ሁኔታዎች አስመልክቶ ጥያቄዎች ካለዎት፣ እባክዎን በመተግበሪያው/ድረ-ገጹ የድጋፍ ክፍል አለዚያም በኢሜል (info@hagerbet.tv) ያግኙን።
10. የአእምሯዊ ንብረት መብቶች - በሃገር ቤት ሚዲያ በኩል የሚቀርቡ ሁሉም ይዘቶች፣ የንግድ ምልክቶች፣ አርማዎች እና ቁሶች የሃገር ቤት ሚዲያ እና የይዘት ፈጣሪዎቹ ብቸኛ ንብረት ናቸው። - ተመዝጋቢ ደንበኞች አንድን ይዘት ለንግድ ላልሆነ፣ ለግል መጠቀሚያነት ብቻ የማግኘት እና የማየት ውሱን፣ ልዩ ያልሆነ፣ እና ለሌላ ወገን የማይተላለፍ መብት ተሰጥቷቸዋል። - ማንኛውም ይዘታችንን የማባዛት፣ የማሰራጨት፣ የማሻሻል ወይም ያለፈቃድ ጥቅም ላይ ማዋል በጥብቅ የተከለከለ እና ህጋዊ እርምጃን ሊያስከትል የሚችል ይሆናል። |