የግላዊነት ፖሊሲ
ሀገር ቤት ሚዲያ እርስዎ ለሚጥሉብን እምነት በሚሰጠው ከፍ ያለ ግምት የተነሳ፣ የግል መረጃዎትን ለመጠበቅ ያለው ቁርጠኝነም ከፍተኛ ነው። ይህ የግላዊነት ፖሊሲ፣ በሞባይል መተግበሪያዎች፣ እንዲሁም በድረ-ገጽ ላይ በአገልግሎቶቻችንን በሚጠቀሙበት ጊዜ፣ መረጃዎን በምን ዐይነት መንገድ እንደምንሰበስብ፣ እንደምንጠቀም እና እንደምንጠብቅ ያብራራል።
1. የምንሰበስበው መረጃ
· የግል መረጃ፡- በምዝገባ ወቅት የሚሞሉ መረጃዎች፣ ማለትም ስም፣ ኢሜይል፣ ስልክ ቁጥር እና የመለያ (account) ዝርዝሮች ።
· የክፍያ መረጃ፡- በታማኝ የሶስተኛ ወገን አቅራቢዎች (እንደ የመተግበሪያ መደብር መለያዎ አቅራቢ) ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ የሚከናወን። የካርድዎን ዝርዝር መረጃዎች አናከማችም።
· የአጠቃቀም መረጃ፡- የመሣሪያ (ዲቫይዝ) ዓይነት፣ የመተግበሪያ ሥሪት፣ አይፒ አድራሻ እና በመተግበሪያው/ድረ-ገጹ ላይ የሚያደርጉት የአሰሳ እንቅስቃሴ።
· ምርጫዎች፡- የቋንቋ ምርጫ (አማርኛ ወይም እንግሊዝኛ)፣ የታየ ይዘት እና የደንበኝነት ምዝገባ እንቅስቃሴ።
2. መረጃዎትን እንዴት እንጠቀማለን
· አገልግሎቶቻችንን ለማቅረብ እና ለማሻሻል።
· የደንበኝነት ምዝገባዎን ለማካሄድ እና መለያዎን ለማስተዳደር።
· ተሞክሮዎን ለግልዎ እንዲስማማ አድርገን ለማበጀት እና ይዘትን ለመጠቆም።
· ድጋፍን፣ ማሻሻያዎችን እና ማስተዋወቂያዎችን በተመለከተ ከእርስዎ ጋር ተግባቦት ለመፍጠር።
· የሚመለከታቸው ህግጋት መከበራቸውን ለማረጋገጥ እና የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመከላከል።
3. የመረጃ ጥበቃ እና ደህንነት
ገንዘብ ነክ መረጃዎን ለመጠበቅ የባንክ ደረጃ ምስጠራዊነት ያላቸው (SSL/TLS) እና ከPCI-DSS ጋር የተጣጣሙ የክፍያ ጌትዌይስ (መስመሮችን) እንጠቀማለን። ውሂብዎ የሚከማቸው የተጠበቀ ተደራሽነት ባላቸው ሰርቨሮች (የመረጃ ቋቶች) ላይ ይሆናል። ስርዓቶቻችንን ከሰርጎ ገቦች፣ ካልተፈቀደ ተደራሽነት እና ከሳይበር ስጋቶች ለመጠበቅ ያለማቋረጥ እንቆጣጠራለን።
4. መረጃ ስለማጋራት
· የግል መረጃዎን ለሶስተኛ ወገኖች አንሸጥም ወይም አናከራይም።
· ለስራ ማስኬጃ ዓላማዎች ብቻ (ለምሳሌ፣ ለክፍያ ማካሄጃ፣ ለማስተናበሪያ አገልግሎቶች) ከታመኑ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር የተወሰነ መጋራት ሊከሰት ይችላል።
· በሕግ ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወይም መብቶቻችንን እና ተጠቃሚዎቻችንን ለመጠበቅ መረጃን ልናሳውቅ እንችላለን።
5. ዓለም አቀፍ ተደራሽነት
· የሃገር ቤት ሚዲያ በአለምአቀፍ ደረጃ የሚገኝ በመሆኑ መረጃዎ በተለያዩ ሀገራት ስራ ሊካሄድበት ይችላል። ይሁን እንጂ በየትኛውም ስፍራ ግላዊነትዎ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ጠንካራ ስርዓቶችን ዘርግተን ነቅተን እንጠብቃለን።
6. መብቶችዎ
· በማንኛውም ጊዜ የግል መረጃዎን ለማግኘት፣ ለማረም ወይም ለመሰረዝ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።
· የደንበኝነት ምዝገባዎን በማንኛውም ጊዜ በመተግበሪያ መደብር መለያ ቅንብሮችዎ ውስጥ መሰረዝ ይችላሉ።
· መለያዎን በማንኛውም ጊዜ በመተግበሪያው (Profile > Delete Account)፣ በድረ-ገጻችን hagerbet.tv/delete-account ላይ፣ ወይም ወደ info@hagerbet.tv ኢሜይል በመላክ መደምሰስ ይችላሉ። ያ ገጽ የምንሰርዘውን እና የምናስቀምጠውን መረጃ ያብራራል።
· ማስተዋወቂያ ኢሜይሎች ወይም ማሳወቂያዎች እንዳይደርስዎት ይቅርብኝ ማለት ይችላሉ።
7. የልጆች ግላዊነት
· የሃገር ቤት ሚዲያ መለያዎች ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ አዋቂዎች ብቻ ናቸው። ልጆች ይዘቶችን ሊመለከቱ የሚችሉት በወላጅ ወይም በአሳዳጊ መለያ እና ቁጥጥር ስር ብቻ ነው። ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች ከሆኑ ልጆች የግል መረጃ እያወቅን አንሰበስብም። አንድ ልጅ የግል መረጃ እንደሰጠን ካመኑ፣ ወደ info@hagerbet.tv ኢሜይል ይላኩልን፤ መረጃውን እንሰርዘዋለን።
8. ያግኙን
ይህንን የግላዊነት ፖሊሲ በሚመለከት ጥያቄዎች ወይም ቅሬታዎች ካሉዎት እባክዎን በመተግበሪያው/ድረ-ገጹ ውስጥ ባለው የድጋፍ ክፍል በኩል ያግኙን ወይም በኢሜል ይላኩልን: info@hagerbet.tv